=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
በአሏህ ስም እጅግ በጣም ርህሩህ በጣም አዛኝ በሆነው።
አንድ አምላክ ብቻ መኖሩን የሚያውጅ ሃይማኖት ቢኖር ኢስላም ብቻ ነው። አንድ ፍፁም አምላክ ሲባል ደግሞ በሁለንተናዊ ባህሪው ፍፁም አምሳያና ሸሪክ(ተጋሪ) የሌለው ብቸኛ አንድ አምላክ ማለት ነው።
--<({አል-ኢኽላስ : 1-4})>--
«በል: እርሱ አሏህ አንድ ነው። አሏህ የሁሉ መጠጊያ ነው። አልወለደም ፤ አልተወለደም። ለርሱም አንድም ቢጤ የለውም።»
ቤኖኒ በምትባል የደቡብ አፍረሪካዊት ከተማ አንድ ሰው ይኖራል። ይህ ሰው በስነ መለኮት ትምህርት የነጠረ ዕውቀት የለውም። ሆኖም ግን ሙስሊሞችን ለማጥመቅ በክርስቶስ የተሾመ የፈጣሪ መልእክተኛ እንደሆነ ደጋግሞ በመለፈፍ ራሱን ያታልላል። በጥብቅና ሙያ የሰለጠ ነው። ይህ ሰው ቅንጣት የአረብኛ ቃል ሳያውቅና ቁርአንን በአግባቡ ሳይረዳ በቃላት በመጫወትና የቅዱስ ቁርአን አንቀፆችን ያለቦታቸው በመጠቃቀስ በማወናበድ ረገድ በጣም የተካነ ነው። ሙስሊሞችን እየሱስ(ኢሳ(ዐ.ሰ)) ፈጣሪ እንደሆነ ለማሳመን ይሻል። ይህ አይነቱ እምነት ደግሞ በአሏህ ፍጹማዊ አንድነት ላይ እምነትታቸውን ለአፀደቁ ሙስሊሞች ከቶውንም የማይዋጥላቸው ብቻ ሳይሆን በአሏህ ሉአላዊና ፍጹማዊ አንድነት ላይ ማሾፍ ሆኖ ይታያቸዋል፤ ስለሆነም ይጠየፋታል። ይህም ብቻ አይደለም በቅዱስ ቁርአን በግልፅ ሠፍሮ የሚገኘውን የአሏህ አዋጅ የሚቃረን ጭምርም በመሆኑም ያወግዙታል። ሆኖም የዚህ መሠሪ ወንጌላዊ ሙስሊሞችን የማታለል ዘዴዎችንና ጥረቶች ሁሉ ያለጥርጥር ይከሽፋሉ። ምክኒያቱም እውነትን በአፈጮሌነት መቀልበስ የሚሞከር አይደለምና። ቅዱስ ቁርአን ይህን አስመልክቶ እንዲህ ይለናል:-
--<({አል-ኢስራእ :81})>--
«በልም እውነት መጣ ፥ ውሸትም ይወገድ ፤ እነሆ ውሸት ተወጋጅ ነውና።»
ሁለት መላምቶች
እየሱስ ጌታ እግዚአብሔር ለመሆኑ ሰውየው ሁለት መላምቶችን በማስረጃነት ያቀርባል። እነሱም:-
1) እየሱስ አምላክ ነው ስንል ወይም እግዚአብሔር እንደሆነ ስንከራከር አብ ነው ማለታችን አይደለም። የጌታን ባህሪይ ይጋራል ለማለት ነው።
2) እየሱስ ከፈጣሪ ጋር ሁለንተናዊ የባህሪ ተመሳሳይነት እንዳለው እርግጥ ነው። ሆኖም ግን አብ አይደለም።
ባጭሩ ሰውየው እየሱስ የእግዚአብሔርን ባህሪ የተላበሰና በሁለመናው የፈጣሪን በባህሪ የሚያንፀባርቅ በመሆኑ በጌትነቱ ልንቀበለው እንደመሚገባ ነው የሚሞግተን። ሰውየው ቀደም ሲል በጨረፍታ እንደጠቀስ ነው የጥብቅና ሙያ ባለቤት በመሆኑ አንዳችም አሳማኝነት በሌላቸው ፍሬ ቢስ ቃላት ብዙ ቅጾችን የመሙላት ችሎታውን አንጠራጠርም። ይህን እሰጥ አገባ አስነስቶ የእየሱስን መለኮታዊነት ለማረጋገጥ የሚጠቀሙባቸው ስልቶች ስለ ጠበቆችና ስለ ጥብቅና ብዙ ከመናገራቸው ውጭ ቁልጭ ያለውን መጽሐፍ ቅዱሳዊ እውነት የሚያረጋግጡ አይደሉም።
ከዚህ በታች ከመጽሐፍ ቅዱስ አያሌ ጥቅሶችን ዋቢ በማድረግ እየሱስ የአምላክን ባህሪ እንደማይጋራና በምንም መልኩ እግዚአብሔርን እንደማይመስል በማመልከት የሰውየው አባባል መሠረተ ቢስ መሆኑን ለማሳየት እንሞክራለን። ጥቅሶቹ ላይ የእኛን አስተያየት ሳንጨምር እንዳሉ አስቀምጠናቸዋል። እስኪ ራሱ መፅሐፍ ቅዱስ እንዲናገር እንፍቀድለት። እየሱስን አምላክ ፈጣሪ እግዚአብሔር ጌታ እንደሆነ መስበክ በፈጣሪ ታላቅነት ላይ ማሾፍ ብቻ ሳይሆን ወደ ክሕደት የመጨረሻ እርከን የሚያሽቀነጥር ነው። የሰው ልጅንም የማመዛዘን ችሎታ የሚያረክስና የሚያኮስስ ስድብ ነው።
ማስታወሻ
ከዚህ በታች የሰፈሩት ጥቅሶች ሕጋዊና ይፋዊ ሥርጭት ካለው መጽሐፍ ቅዱስ ነው። በርዕሶቻችንና በንዑስ ርዕሶቻችን ውስጥ አምላክ የሚለውን ቃል በትምህርተ ጥቅስ አስቀምጠናል። ይህም እየሱስ አምላክ ነው የሚለውን ጭፍን እምነት የማንቀበል መሆናችንን ለማስመልከት ነው። እየሱስ በሚለው ቦታ አምላክ የሚለውን ቃል እየተካን እየሱስና አምላክ ተመሳሳይ መሆናቸውን ወይም አለመሆናቸውን እናመሳክር።
የአምላክ ልደት!
«አምላክ ከዳዊት ዘር መፈጠሩን ለማመልከት ፥ በሥጋ ከዳዊት ዘር ስለተወለደ» {ወደ ሮሜ ሰዎች 1:3}
«ነብይ ስለሆነ ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፍኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሃላ እንደማለለት ስለአወቀ፤» {የሐዋሪያት ሥራ 2:30}
የአምላክ የዘር ሐረግ!
«የዳዊት ልጅ የአብርሃም ልጅ የእየሱስ ክርስቶስ ትውልድ መጽሐፍ» {ማቴዎስ 1:1}
የአምላክ ፆታ!
«ሊገርዙት ስምንት ቀን በሞላ ጊዜ በማህፀን ሳይረገዝ በመልአኩ እንደተባለ ፥ ስሙ እየሱስ ተብሎ ተጠራ።» {ሉቃስ 2-21}
ማሪያም አምላክን ስለ መፀነሷ እና ስለ መውለዷ
እንዴት ነው ማሪያም አምላክን አርግዛ የወለደችው፦ ማሪያም እንደ ማንኛዋም ሴት አርግዛ በቀኗ እንደወለደችው ለማመልከት፦
«በዚያም ሳሉ የመውለጃዋ ወራት ደረሰ የበኩር ልጅዋንም ወለደች።» {ሉቃስ 2:6}
ይህም ማለት ማሪያም ተፈጥሯዊ የፅንስ ወራቷን እንደማንኛዋም ሴት መፈፀሟን እንረዳለን። የአወላለዷም ሁኔታ በማንኛቸውም መለኪያ ቢሆን ከመሰል ሴቶች የተለየ አልነበረም።
«እርሷም ፀንሳ ነበር ምጥም ተይዛ ልትወልድ ተጨንቃ ጮኸች።» {የዩሐንስ ራዕይ 12:2}
አምላክ የሴት ጡት ጠብቷል!
«ይህንም ሲናገር ከህዝቡ አንዲት ሴት ድምፅዋን ከፍ አድርጋ የተሸከመችህ ማህፀንና የጠባሃቸው ጡቶች ብፁዓን ናቸው አለችው።» {ሉቃስ 11:27}
የአምላክ የትውልድ መንደር!
«እየሱስም በይሁዳ ቤተልሔም በንጉሱ በሄሮድስ ዘመን በተወለደ ጊዜ፥» {ማቴዎስ 2:1}
የአምላክ ሙያ!
«ይህ ጸራቢው የማሪያም ልጅ የያዕቆብም ፣ የዮሳም ፣ የይሁዳም ፣ የስምዖንም ወንድም አይደለምን?» {
ማርቆስ 6:3}
«የጸራቢ ልጅ አይደለምን?» {ማቴዎስ 13:55}
የአምላክ የመጓጓዣ ዘዴ!
«ለጽዮን ልጅ እነሆ ንጉሥሽ የዋህ ሆኖ በአህያ ላይና በአህያይቱ ግልገል በውርንጭ ላይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል በሉአት» {ማቴዎስ 21:5}
«እየሱስ ውርንጫ አግኝቶ በእርሱ ተቀመጠ።» {ዩሐንስ 12:15}
የአምላክ ምግብና አስካሪ መጠጥ
«የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጣ እርሱም እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ የቀራጮችና የሃጢያተኞች ወዳጅ ይሉታል።» {ማቴዎስ 11:19}
«የሰው ልጅ እየበላና እየጠጣ መጥቷልና እነሆ በላተኛና የወይን ጠጅ ጠጭ የቀራጮችና የሃጢያተኞች ወዳጅ» {ሉቃስ 7:34}
የአምላክ ድህነት!
«እየሱስም ለቀበሮዎች ጉድጓድ ለሰማይም ወፎች መስፈሪያ አላቸው ፤ ለሰው ልጅ ግን ራሱን የሚያስጠጋበት የለውም አለው።» {ማቴዎስ 8:20}
የአምላክ ቁሳቁሶች!
«......የጫማው ጠፍር......» {ሉቃስ 3:16}
«ጭፍሮቹም እየሱስን በሰቀሉት ጊዜ ልብሶቹን ወስደው ለእያንዳንዱ ጭፋራ አንድ ክፍል ሆኖ በአራት ከፋፈሉት እጀ ጠባቡንም ደግሞ ወሰዱ።» {ዩሐንስ 19:23}
አማኝ ይሁዳዊ አምላክ!
«ማለዳም ተነስቶ ገና ሌሊት ሳለ ወጣ ወደ ምድረ በዳም ሄዶ በዚያ ፀለየ።» {ማርቆስ 1:35}
መልካም ዜጋና ለቄሳርም ታማኝ አምላክ
«የቄሣርን ለቄሣር ፥ የእግዚያቢሔርንም ለእግዚያቢሔር አስረክቡላቸው።» {ማቴዎስ 22:21}
ግብር ከፋይ አምላክ!
«ወደ ቅፍርናሆምም በመጡ ጊዜ ግብር የሚቀበሉ ሰዎች ወደ ዼጥሮስ ቀረቡና መምህራችሁ ሁለቱን ዲናር አይገብርምን አሉት አዎን ይገብራል አለ።» {ማቴዎስ 17:24-25}
የአምላክ ቤተሰብ!
«አምላክ የዮሴፍ ልጅ ነበር፦ ፊልዾስ ናትናኤልን አግኝቶ ሙሴ በሕገ-ነቢያትም ስለ እርሱ የጻፉትን የዮሴፍን ልጅ የናዝሬቱን እየሱስን አግኝተነዋል አለው።» {ዩሐንስ 1:46}
የአምላክ ወንድሞች!
«ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በመምኩራባቸው ያስተምራቸው ነበር። እንዲህም አሉ ይህን ጥበብና ተዓምራት ከወዴት አገኘው? ይህ የጸራቢ ልጅ አይደለምን? እናቱስ ማሪያም ትባል የለምን? ወንድሞቹስ ያዕቆብና ዮሳ ስምዖንም ይሁዳም አይደሉምን? እህቶቹስ ሁሉ በእኛ ዘንድ ያሉ አይደሉምን?» {ማቴዎስ 13:54-56}
የአምላክ መንፈሳዊ እድገት!
«ሕፃኑም ጥበብም ሞልቶበት በመንፈስ ጠነከረ።» {ሉቃስ 2:40}
የአምላክ አእምሮአዊ አካላዊ ባህርያት እድገት
«እየሱስም ደግሞ በጥበብና በቁመት በሞገስም በእግዚያአብሔርና በሰው ፊት ያድግ ነበር።» {ሉቃስ 2:52}
ወላጆቹ ወደ እየሩስአሌም ሲወስዱት አምላክ 12 ዓመት ሞልቶት ነበር። «ወላጆቹም በየአመቱ በፋሲካ በአል ወደ እየሩስ አሌም ይወጡ ነበር።የአሥራ ሁለት አመት ልጅ በሆነ ጊዜ እንደ በዓሉ ሥርአት ወደ እየሩስ አሌም ወጡ።» {ሉቃስ 2:41-42}
አቅመ ቢስ አምላክ!
«እኔ ከራሴ አንዳች ላደርግ አይቻለኝም ፤ እንደሰማሁ እፈርዳለሁ ፍርዴም ቅን ነው፤ የላከኝን ፈቃድ እንጂ ፈቃዴን አልሻምና።» {ዩሐንስ 5:30}
አምላክ ስለምፅዓት አያውቅም!
«ስለዚያች ቀን ወይም ስለዚያች ሰዓት ግን የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን ከአባት በቀር የሚያውቅ የለም።» {ማርቆስ 13:32}
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|